Psalm 138 | In Amharic and English (with Amharic MP3)
መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #138
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 138 |
Psalm 138 |
1 አቤቱ፥ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፥ የአፌን ነገር ሰምተኸኛልና በመላእክት ፊት እዘምርልሃለሁ። |
1 I will praise thee with my whole heart: before the gods will I sing praise unto thee. |
2 ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህ ስምህንም አመሰግናለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና። |
2 I will worship toward thy holy temple, and praise thy name for thy lovingkindness and for thy truth: for thou hast magnified thy word above all thy name. |
3 በጠራሁህ ቀን በፍጥነት አድምጠኝ ነፍሴን በኃይልህ በብዙ አጸናሃት። |
3 In the day when I cried thou answeredst me, and strengthenedst me with strength in my soul. |
4 አቤቱ፥ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያመሰግኑሃል የአፍህን ቃል ሁሉ ሰምተዋልና። |
4 All the kings of the earth shall praise thee, O Lord, when they hear the words of thy mouth. |
5 በእግዚአብሔርም መንገድ ይዘምራሉ የእግዚአብሔር ክብር ታላቅ ነውና። |
5 Yea, they shall sing in the ways of the Lord: for great is the glory of the Lord. |
6 እግዚአብሔር ከፍ ያለ ነውና፥ ወደ ችግረኞችም ይመለከታልና ትዕቢተኞችንም ከሩቅ ያውቃል። |
6 Though the Lord be high, yet hath he respect unto the lowly: but the proud he knoweth afar off. |
7 በመከራ መካከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ሕያው ታደርገኛለህ በጠላቶቼ ቍጣ ላይ እጆቼን ትዘረጋለህ፥ ቀኝህም ታድነኛለች። |
7 Though I walk in the midst of trouble, thou wilt revive me: thou shalt stretch forth thine hand against the wrath of mine enemies, and thy right hand shall save me. |
8 እግዚአብሔር ብድራትን ይመልስልኛል አቤቱ፥ ምሕረትህ ለዘላለም ነው አቤቱ፥ የእጅህን ሥራ ቸል አትበል። |
8 The Lord will perfect that which concerneth me: thy mercy, O Lord, endureth for ever: forsake not the works of thine own hands. |